No Image Available

ዘላቂ ሰላም ኢትዮጵያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው

 Category: Op-ed More Details  Download
 Description:

ከልጅነቴ ነፍስ ካወቅኩበት ከ1970ዎቹ ጊዜ ጀምሮ ስሰማ ያደግኩት እስካሁንም የሚሰማው በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን የአንድ አህጉር ልጆች ብሎም ከአንድ አብራክ የተገኙ ወንድማማቾች እና እህትቶማማቾች መካከል ትርጉም የለሽ እና አረመኔያዊ እርስ በርስ ግጭት እንደ ጠላት በመፈራረጅ ለእልቂት ተዳርገዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአፍሪካ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣በሴራሊዮን ፣ በላይቤሪያ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በአንጎላ እና በማሊ የእርስ በርስ ጦርነት ይካሄድ ነበር። በተጨማሪም በፍልስጤም፣ በኢራቅ፣ በኢራን፣ በእስራኤል፣ በፓኪስታን፣ በአፍጋኒስታን እና በካሽሚር የተደረጉ የጦርነት ድራማዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በዜናዎች ላይ አዕምሯችንን የያዙ ነበሩ። አሁንም አንዳንዶቹ ሰላም ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ ከጦርነት ክፉ አባዜ ወይም አዙሪት ለመውጣት ጥረት ያደርጋሉ ወይም አልቻሉም።